ይህ ጥቅል ሥልጠና መሠረታዊ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታን ለማወቅ ይረዳል፡፡ በእዚህ ሥልጠና መሠረታዊ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ቁጥር ፩ እና ፪ በአንድ ላይ ተካተዋል፡፡
ሥልጠናውን ሲጨርሱ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ምንነትን፣ የህግ ጉዳዮቹን፣ መሠረታዊ የሰውነት ክፍሎች አወቃቀርና አሰራርን፣ ተጎጂን በሶስቱ የ”መ” ህጎች መመርመርን፣ መሠረታዊ ሕይወት አድን ሕክምናን፣ የአየር ቧንቧ አከፋፈትና ትንፋሽ አሰጣጥን፣ ደም የማቆም ጥበብን፣ ተጎጂን የማጓጓዝ ዘዴን እና የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ሳጥን አጠቃቀምን በተገቢው ሁኔታ ይረዳሉ፡፡